የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 4 ግዙፍ ፕሮጀክቶች አስመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 4 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

ለምረቃ የበቁት እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፦ ዘመናዊ የዳታ ሴንተር (የመረጃና የቴክኖሎጂ ቋት)፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየም፣ የእንስሳት ህክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል እና የመምህራን የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች (አፓርታማዎች) ናቸው።

በምረቃ መርሀ- ግብሩ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንደገለፁት የእንስሳት ህክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል በሀገሪቱና በአካባቢው ያለውን እምቅ የእንስሳት ሀብት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

የማህበረሰቡ የኑሮ ዋስትና ለሆኑት እንስሳት የጤና ዋስትና ከመስጠቱ ባለፈ፣ ለእንስሳት ህክምና ሳይንስ (Veterinary Science) ዘመናዊ ማስተማሪያና የምርምር ማዕከል ሆኖ ያገለግላልም ሲሉ ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ በአይነቱ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካም ጭምር ልዩና ብቸኛ መሆኑ ገልጸዋል።

ዘመናዊው የዳታ ሴንተር የዩኒቨርሲቲውን የዲጂታልና የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።

ሌላው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማዎች የቀድሞውን የተማሪዎች ዶርሚተሪ ወደ መምህራን መኖሪያነት በመቀየር የወጪ ቆጣቢነትና የሀብት አጠቃቀም ብልሃትን በተግባር ያሳየ እንደሆነ ተናግረዋል።

የስፖርት ማዕከሉ ደግሞ የተማሪዎችን ጤናማ ሕይወት ከመደገፍ ባለፈ በዩኒቨርሲቲውና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክርም ገልፀዋል::

የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ- ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት ሚኒስቴር ጥራት ያለው ከፍተኛ ትምህርትን፣ በተግባር የተደገፈ ምርምርንና ማህበረሰብ-አቀፍ አገልግሎትን ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ደረጀ አረጋኸኝ በበኩላቸው ግንባታዎቹ በጥራት ተጠናቀው ለዚህ መብቃታቸው በቅንጅት የመስራት ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#ጎንደርዩኒቨርስቲፕሮጀክት
#ትምህርትሚኒስትር
#የኢትዮጵያኮንስትራክሽንባለስልጣን
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2