ባይናንስ የኢትዮጵያ ብር በፕላትፎርሙ ላይ እንደማይገኝ አረጋገጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ድረ-ገጽ ባይናንስ (Binance) በኢትዮጵያ አገልግሎት ስለመጀመሩ በተሰራጨው መረጃ ላይ ማስተካከያ ሰጥቷል። ኩባንያው የኢትዮጵያ ብር በድረ-ገጹ ላይ እንደማይገኝ በግልጽ አስታውቋል።

​ከዚህ ቀደም የባይናንስ ፕላትፎርም በኢትዮቴሌኮም በኩል በኢትዮጵያ ተደራሽ እንደሆነ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ባይናንስ ለብርሜትሪክስ በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ ብር (ETB) በፕላትፎርሙ ላይ እንደማይገኝ አረጋግጧል። ኩባንያው ይህ ውሳኔ የሀገሪቱን የቁጥጥር መመሪያዎች መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጿል።

​ባይናንስ አክሎም በኢትዮጵያ የሚሰጡ መመሪያዎችን እና ህጎችን ለማክበር ቁርጠኛ እንደሆነና ለተጠቃሚዎች ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ገልጿል። ይሁን እንጂ የፕላትፎርሙ አጠቃላይ ተደራሽነት በኢትዮቴሌኮም በኩል ስለመመለሱ ወይም አለመመለሱ የሰጠው ግልጽ ማብራሪያ የለም።

​በኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የኢትዮጵያ ብር ብቸኛው ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ ነው። ባንኩ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳስጠነቀቀው፣ ያለፈቃድ የሚፈጸሙ የቨርቹዋል ንብረት ግብይቶች ህጋዊ እውቅና የላቸውም።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1