#Ethiopia | የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ሆስፒታል የጆይንት ኮሚሽን ኢንተርናሽናል (JCI) ዓለም አቀፍ የጥራት እውቅናን አገኘ።
ይህንን አስመልክቶ በተዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ሆስፒታሉ የላቀ የህክምና ደረጃን አሟልቶ ይህንን ታሪካዊ እውቅና ማግኘቱ ለሀገሪቱ የጤና ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ገልጸዋል። እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የጤና ተቋማት መበራከታቸው የህክምና አገልግሎት ጥራትን ከማሳደግ ባለፈ፣ ኢትዮጵያን ተመራጭ የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።
ሚኒስትሯ በመልዕክታቸው እንደጠቆሙት፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ የጤና ተቋማት የመንግሥትን የጤና ዘርፍ ማሻሻያና የአክሬዲቴሽን ፖሊሲዎች ፍሬ እያፈሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
የጤና ሚኒስቴርም በመላ ሀገሪቱ የአክሬዲቴሽን ሥርዓትን ለማጠናከር በትጋት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ሕዝቡ የሚመጥነውን የላቀ አገልግሎት ለመስጠት በተቋማት መካከል ጤናማ የጥራት ውድድር መፈጠሩ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ወደፊትም መንግሥት የግል የጤና ተቋማት አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ፣ እንዲስፋፉ እና ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን እንዲያሟሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።
በዕለቱ የተቋሙ የህክምና እና የድጋፍ ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን፣ ሆስፒታሉ ለዚህ ታላቅ የዓለም አቀፍ እውቅና ማዕረግ እንዲበቃ ሌት ተቀን የደከሙና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና የሥራ ቡድኖች ተገቢው እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ




Source: GetuTemesgen









No comments yet.