‎የአንድ ጀግና አባት ህልፈት የትናንት ጉልበት የዛሬው የቤተሰብ ጣጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

👉ሼር በማድረግ ተባበሩ

ባሳለፍነው ሳምንት ‎​ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. የተሰማው መራር ዜና፣ የብዙዎችን ልብ ሰብሮ አልፏል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሚዲያ ኃላፊ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (አዲስ ቴሌቪዥን) ጋዜጠኛ የነበረው ሳህለገብርኤል፤ ለሀገሩ፣ ለሙያው እና ለቤተሰቡ የነበረው ቁርጠኝነት አርአያ የሚባል ነበር።

‎ለ20 ዓመታት በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ውስጥ ፍትህን ለማስፈንና የህግ ታራሚዎችን ለመቅረጽ የነበረው ጉልበትና እውቀት፤ ከሙያው ባለፈ ለሀገር የነበረው ፍቅር መገለጫ ነበር።

‎በተለይም ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያሳየው ትጋት፣ በጋዜጠኝነት ሙያው ውስጥ ለተተኪዎች ትልቅ ትምህርት ነው።

‎​ከሞቱ ሁለት ቀናት በፊት እንኳ ለተቋሙ ማሻሻያ ትልቅ እቅድ አውጥቶ የነበረው ሳህለገብርኤል፣ ዛሬ በሞት ተነጥቆ የሶስት የዋህ ልጆች አባትና ባለቤቱን በከፍተኛ ሁኔታ ጥሎ አልፏል።

‎የዛሬው አሳዛኝ እውነታ ግን የሞቱ ዜና ብቻ ሳይሆን፣ ከኋላው የቀሩት ቤተሰቦቹ በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ መውደቃቸው ነው።

‎ጋዜጠኛ ሳህለገብርኤል በህይወት በነበረበት ወቅት ለሌሎች የነበረው ደግነት፣ ዛሬ ለቤተሰቡ መመለስ አለበት። በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የአባሎች መኖሪያ ካምፕ የሚኖሩት ቤተሰቦቹ፣ የወደፊታቸው እጅግ አሳሳቢ ሆኗል።

‎​ለልጆቹ መኖሪያ፡ መጠለያ ማግኘት አቅማቸው በላይ ሆኗል።
‎​የልጆቹ የወደፊት ተስፋ የሆነው ትምህርት እንዲቀጥል ድጋፍ ይፈልጋሉ።
‎​በበዓላት እና በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ከጎናቸው የሚቆም ሰው ይሻሉ።

‎​ይህ ጥሪ ለክቡርት ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ለፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ፣ ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች እና ለሰብአዊነት ለሚቆሙ ወገኖች ሁሉ የሚቀርብ የአደራ ጥሪ ነው።
‎​አጋርነታችሁን ግለጹ

‎የሳህለገብርኤልን አሻራ ለማስታወስ እና ቤተሰቡን ከመከራ ለመታደግ፣ ያላችሁን ትንሽ ድጋፍ እንድትለግሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

‎​ባንክ: ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)

‎​የሂሳብ ቁጥር: 1000081155457
‎​
ሙሉ ስም: ጎጃም ይበልጣል ከበደ

‎​ለቤተሰቦቹ የምናደርገው እያንዳንዱ እርዳታ፣ የጀግናውን ጋዜጠኛ ነፍስ የሚያሳርፍ፣ ለልጆቹ ደግሞ ተስፋን የሚሰጥ ነው።

#ሼርርርርርር





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: