#Ethiopia | የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 11ኛውን ሀገር አቀፍ የስፖርት ሳይንስ የጥናትና ምርምር ጉባዔ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
በጉባዔው የተገኙት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ለውጥ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል።
የስፖርት ሪፎርም ሰነዶች ወደ ትግበራ መግባታቸው ዘርፉ የነበሩ የአመራርና የአሠራር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መሠረት እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፣ ሪፎርሙ ጤናማና አምራች ዜጋ መፍጠር፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና ተወዳዳሪ አሸናፊ ትውልድ ማፍራትን ዋና ግቦች አድርጎ ይዟል።
በተጨማሪም አዲስ የስፖርት ፖሊሲና የስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ መጽደቃቸው ዘርፉን በህግና በስርዓት ለመምራት አስፈላጊ መሠረት እንደፈጠረ ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ስፖርት ወንድማማችነትን፣ አብሮነትን፣ ፍቅርና ሰላምን የሚያጎለብት በመሆኑ በሀገር ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰው፣ ባለሙያዎችም እውቀታቸውን በቀጣይነት በማሳደግ ዘመናዊ አሠራሮችን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አንበሳው እንየው በበኩላቸው፣ አካዳሚው ባለፉት 11 ዓመታት 159 የስፖርት ጥናቶችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
ከእነዚህ 45ቱ በአካዳሚው በራሱ አቅም የተከናወኑ ሲሆን፣ 114ቱ ደግሞ በተባባሪ ተመራማሪዎች የተጠኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በአዳማ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ሀገር አቀፍ ጉባዔ 12 የስፖርት ሳይንስ ጥናቶች ለተሳታፊዎች ቀርበው በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
#Ethiopia #Sports #EthiopianSportsAcademy #SportsScience #Research #Adama #Getu



Source: GetuTemesgen









No comments yet.