ፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት 150 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን 8.2 ቢሊዮን ብር በሚገመት ወጪ ሊገዛ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

ፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት ለከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ድንበር ከሚጋሩ የጎረቤት ሐገራት ጋር ወደፊት ለሚጀመረው የየብስ ትራንስፖርት ይውላሉ ያላቸውን 150 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ለመግዛት ማቀዱን አስታውቋል።

አሁን ባለው ገበያ የአንድ አውቶቡስ ዋጋ 55 ሚሊዮን ብር አካባቢ ይገመታል ተብሏል።

የተቋሙ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታዲዮስ ሌራ፣ “ግዢውን ለመፈጸም በማኔጅመንት ደረጃ ውሳኔ ተላልፏል” ሲሉ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል።

የማኔጅመንቱ ውሳኔ በቀጣይ በቦርድ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል። እቅዱን ወደ ተግባር ለመቀየር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተከናወኑ እንደሆነም አስረድተዋል።

ክፍያው በ2 ዙር ማለትም፣ ከአውቶቡሶቹ ጠቅላላ ዋጋ 50 በመቶውን በዚህ በጀት ዓመት፣ ቀሪውን 50 በመቶ ክፍያ ደግሞ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ለማጠናቀቅ ተወስኗል ተብሏል።

አውቶቡሶቹ የከተማ ትራንስፖርት እጥረትን ለማቃለል እንዲሁም፤ ወደ ፊትም ከኢትዮጵያ ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገራት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል። በተጨማሪም፤ በሀገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ እቅድ ተይዞላቸዋል ተብሏል።

በቅርቡ ግዢአቸው እንደሚፈጸም የሚጠበቀው የኤሌክትሪክ አውቶቡሶቹ የነዳጅ ወጪን ይቀንሳሉ ቢባልም የባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን የተመለከተው መረጃ አልተገለጸም።

#አሐዱ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1