አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረው የልጅ ልጆችም ያዩት የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ እናት ከላይ በምስሉ የምታ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረው የልጅ ልጆችም ያዩት የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ እናት

ከላይ በምስሉ የምታያቸው ወ/ሮ አልማዝ አሻራው ይባላሉ። በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በቤተሰብ ጫና ምክንያት በ1982 ዓ.ም ከ4ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።
በ1983 ዓ.ም ትዳር የመሰረቱት ወ/ሮ አልማዝ የስምንት ልጆች እናት ናቸው። አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረዋል፣ የልጅ ልጆችም አይተዋል።
የቀሩት አራት ልጆቻቸው ደግሞ ከ5ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ትምህርታቸውን ዳግም መማር ያሰቡት ትላንት ያላሳኩትን፣ ያልኖሩትን ህልማቸውን ዳግም ለመኖር እንደሆነ ወ/ሮ አልማዝ ይገልጻሉ።
እኚህ ብርቱ እናት ዘንድሮ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው፣ በመጀመሪያው ዙር በበይነ መረብ ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል። ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ተምረው መመረቅ ህልማቸው እንደሆነም ይናገራሉ።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1