ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የመስማት ችግር አለባቸው!

- Advertisement -
Sidebar AD

~ የጤና ድርጅት

#Ethiopia | የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በመላው አለም ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የመስማት ችግር አለባቸው ብሏል።

ይሁን እንጂ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ምርመራ የማግኘት እድል እንደሌለውም ገልጿል።

የጤና ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በየጊዜው የሚደረግ የህክምና ምርመራ ለችግሩ ዋነኛ መፍትሔ ነው ይላሉ።

በተለይም በገጠርና መሰረተ ልማት በማይደርስባቸው አካባቢዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመስማት ችግርን በቶሎ መለየት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በልጆች ላይ የሚከሰት የመስማት ችግርን በወቅቱ መለየት ከተቻለ ለቋንቋና ለአዕምሮ እድገታቸው ወሳኝ መሆኑንም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።

ባላደጉ ሀገራት ችግሩ የከፋ መሆኑን የገለፀው የአለም ጤና ድርጅት አብዛኛዎቹ ሀገራት ለዜጎቻቸው የጆሮ ቅድመ ምርመራ እንደማያደርጉ ገልጿል።

የመስማት ችግር ቀላሉ መከላከያ መንገዱ አስቀድሞ ምርመራ ማድረግ እንደሆነ ነው ድርጅቱ የገለፀው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

​#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Worldhealthorganization
#Hearingproblems


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: