ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን ተከላካይ ጄረሚ ዣኬን አስፈረመ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ሊቨርፑል ከፈረንሳዩ ስታድ ሬንስ ክለብ የ20 ዓመቱን ተከላካይ ጄረሚ ዣኬን በረጅም ጊዜ ውል ማዘዋወሩን በይፋ አረጋግጧል። ክለቡ ከዚህ ወጣት ፈረንሳዊ ተጫዋች ጋር ቀደም ብሎ ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ሲሆን ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓጉሏል ፤ አሁን ምሉዕ የውል ሂደቱ የተጠናቀቀ በመሆኑ ዝውውሩ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ጸድቆ ወደ ሜዳ ያመራል።

በሬንስ የወጣቶች አካዳሚ አድጎ ለዋናው ቡድን 33 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው ይህ ተስፈኛ የመሐል ተከላካይ ባለፈው የ2025-26 የውድድር ዓመት 21 ጨዋታዎችን ማድረጉ የሚታወስ ቢሆንም በየካቲት ወር በደረሰበት የትከሻ ጉዳት ምክንያት የውድድር ዘመኑን ቀድሞ ማጠናቀቅ ችሏል።

​የፈረንሳይ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባል የሆነው ዣኬ ቀደም ሲል በክሌርሞን ፉት ክለብ በውሰት በቆየባቸው 12 ወራት ውስጥ 24 ጨዋታዎችን በማድረግ ጠቃሚ የሜዳ ላይ ልምዶችን ማካበት ችሏል።

በአንፊልድ አዲሱን የእግር ኳስ ጉዞውን ለመጀመር በከፍተኛ ጉጉት ላይ የሚገኘው ተጫዋቹ ለሊቨርፑል ድረ-ገጽ በሰጠው አስተያየት እንደ ሊቨርፑል ባሉ ታላላቅ ክለቦች ውስጥ መጫወት ትልቅ ሕልሙ እንደነበረና አዲሱን ፈታኝ ሕይወት ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን በደስታ ገልጿል።

የዣኬ አዲሱ የሊቨርፑል ማሊያ ቁጥርም በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ለደጋፊዎች ይፋ እንደሚደረግ ክለቡ አስታውቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: