በድሬዳዋ ሐብታቸውን ለመውረስ አባቱን የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ ተፈረደበትተባባሪው ደግሞ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በድሬዳዋ ሐብታቸውን ለመውረስ አባቱን የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ ተፈረደበት
👉ተባባሪው ደግሞ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
​ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ አንደኛ ተከሳሽ ቤካ ኑረዲን ከአዲስ አበባ በምስጢር መጥቶ ከጓደኛው ሊበን ወንደሰን ጋር በመሆን አባቱን ማሪያም ኮንዶሚኒየም አካባቢ በጭካኔ ገድሏል።
ወንጀለኞቹ ድርጊቱን ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ በግል መኪና ቢሰወሩም፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ባደረገው ረቂቅ ክትትል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
​የፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ያቀረበውን ጠንካራ የሰውና የሰነድ ማስረጃ የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ውሳኔውን አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት በዋና ወንጀለኛው ቤካ ላይ የሞት ፍርድ፣ በተባባሪው ሊበን ላይ ደግሞ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: