“አረጋዊው እና ባህሩ”

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በፈረንሳይ ሞርሌ ከተማ “ኤሮ” በተሰኘው የጥበብ ባለሙያ የተሳለውና “አረጋዊው እና ባህሩ ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ የግድግዳ ላይ ሥዕል የበርካቶችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።

ይህ በጥቁርና ነጭ ቀለማት ብቻ ያሸበረቀው ማራኪ የጥበብ ሥራ፤ አረጋዊ ባህረኛን የባህር ላይ ወፍን፣ የመብራት ማማን፣ አለቶችን፣ ጉምና ማዕበሎችን በአንድ ያረጀ ግድግዳ ላይ አዋህዶ በማቅረብ የከተማዋን ጥንታዊ የወደብ ላይ ትዝታዎች በሚያስደምም ሁኔታ ሕያው አድርጎታል።

​የዚህ ድንቅ የጥበብ ሥራ ርዕስ ዓለም አቀፍ ሥነ-ጽሑፍንና የአካባቢውን ታሪክ በአንድ ላይ ያሰናሰለ መሆኑ ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል።

በስያሜው ላይ የተጠቀሰው ሐረግ እ.ኤ.አ. በ1953 በልብወለድ ዘርፍ የፑሊትዘር ሽልማትን ያሸነፈውን ታዋቂውን የኧርነስት ሄሚንግዌይ ታሪክ የሚያስታውስ ሲሆን ሥዕሉ የሞርሌ ከተማ ከዚህ ቀደም የነበራትን ታላቅ የባህር ላይ ንግድ ማዕከልነት ታሪክ በሚገባ የሚዘክር መሆኑ ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: