* የሚከራይ ውሻ አለ!

- Advertisement -
Sidebar AD

* ቻይኖች የሚከራይ ውሻ አለ እያሉ ይገኛል

#Ethiopia | በቻይና የቤት ውሾችን ለእንግዳ ሰዎች በሰዓት ማከራየትና አብረዋቸው እንዲጓዙና እንዲጫወቱ የሚያስችል አዲስ አሰራር ተጀመረ።

ሆኖም ይህ አገልግሎት በእንስሳት መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስከትሎባቸዋል።

“ዋንግቡ” የተሰኘውና በቅርቡ ይፋ የሆነው ይህ የዲጂታል መተግበሪያ የውሻ ባለቤቶች ስለሚያከራዩት ውሻ ሙሉ መረጃ በመተግበርያው ላይ በመጫን ማከራየት ይችላሉ።

የውሻ ፍቅር ኖሯቸው በተለያዩ ምክንያቶች ማሳደግ ያልቻሉ ተከራዮች ደግሞ እንደ ውሻው ዝርያና እንደ ቆይታው በሰዓት ከ10 እስከ 60 ዩዋን ይጠየቃሉ።

ተከራዮች ክፍያውን በመተግበርያው ከፈጸሙ በኋላ ውሾቹን ተረክበው ማናፈስና አብረው ጊዜ ማሳለፍ ይችላሉ ተብሏል።

የመተግበሪያው አዘጋጆች አሰራሩ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የተከራዮችን ትክክለኛ ማንነት እንደሚያረጋግጡ የጂፒኤስ መከታተያ እንደሚጠቀሙና የኢንሹራንስ ዋስትና እንዳለውም ገልጸዋል።

ይህ አገልግሎት በተለይ በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ በስራና በትምህርት ጫና ለተወጠሩ ሰዎች የአእምሮ እረፍትና መዝናኛ እንደሚሰጥ ተነግሯል።

እንዲሁም ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ውሾችን ማሳደግ ለማይችሉ ሰዎች ጥሩ አማራጭ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በሌላ በኩል የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎችና ተሟጋቾች በበኩላቸው ውሾች የማያውቁትን ሰውና አካባቢ እንዲለምዱ መገደዳቸው ከፍተኛ የአእምሮ ጫና እና ፍርሃት እንዲፈጥርባቸው ያደርጋል ብለዋል።

ይህ አሰራር ውሾቹ በኪራይ ቆይታቸው ወቅት ቢጠፉ ቢጎዱ ወይም በሰዎች ላይ ጥቃት ቢያደርሱ ተጠያቂነቱ በማን ላይ እንደሚሆን ግልጽ የህግ ማዕቀፍ የሌለው መሆኑም ሌላኛው አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል ሲል የዘገበው ኦዲቲ ሴንትራል ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#China #DogRentalPlatform
#Additycentral


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: