ልጆቻችን በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከሉ፥ ፍሬያቸውን በጊዜያቸው እንዲሰጡ፡ ቅጠላቸውም እንደማይረግፍ ዛፍ እንዲሆኑ ለቤተሰብ፡ ለሐገር እና ለዓለም እንዲጠቅሙ። የጥበባት ባሕር ቅድስት ቤተ ክርስትያን እቅፍ ውስጥ እናስገባቸው።
ቅዱስ አግናጥዮስ የአዳጊና የወጣቶች የክረምት አዳሪና ተመላለሽ ስልጠና ለሁለተኛ ዙር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/ለአዳሪ/እና በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች/ለተመላላሽ/ ለማሰልጠን ዝግጅታችንን አጠናቅቀን የልጆቻችንን መምጣት እንጠባበቃለን።
በሥልጠናው፦
1. መሠረታዊ የቤተክርስቲያን እውቀትን ይማራሉ ፣
2. ተግባራዊ ክርስትናን በሕይወት መኖርን ይለማመዳሉ ፣
3. መሠረታዊ የሆኑ የሕይወት ክህሎትን ያዳብራሉ፣
4. ዘመናዊነትን በመንፈሳዊ ሚዛን መዝኖ መኖርን ይረዳሉ ፣
5. ምግባር ከሃይማኖት የተስማማላቸው ነገ ሀገራቸውን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በታማኝነት የሚያገለግሉ ይሆናሉ።
የመመዝገቢያ መስፈርት፦
በአዳሪ ከ9 እስከ 17 ዕድሜ ላለቸው
በተመላላሽ ከ7 እስከ 17 ዕድሜ ላላቸው
የልደት ካርድ ማቅረብ የሚችሉ
ልዩ ድጋፍ የሚፈልግ የጤና ችግር ወይም የሕክምና ክትትል የሌለው/ላት
ወላጆች የኢ/ኦ/ቤ/ክ የአባልነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
የትምህርትና ሥልጠና ማእከሉ የሚያወጣውን ደንቦች እና አሠራሮች የሚያከብሩ
በምዝገባ ላይ ነን
ያሉን ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ
ለበለጠ መረጃ 0991333377-0939942222 -0939952222 ይደውሉ
“እውቀትን በምግባር የዋጀ ትውልድ እናፈራለን”
Source: GetuTemesgen









No comments yet.