አዲስ የቡና ጥናት‼️
ቡናን በየቀኑ አብዝቶ መጠጣት ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
አዩዘሀበሻ የጥናቱን ውጤት እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲናይ የሕክምና ማዕከል ከቡና ጋር በተያያዘ በተሰራው አዲስ ጥናት ቡናን አብዝቶ መጠቀም ጭምር ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
ቡና የሚሰጠው ጥቅም በውስጡ ከያዘው ካፌይን ሳይሆን በያዘው ከፍተኛ አንቲ-ኦክሲዳንት ነው።
ቡና ከፍተኛ ፀረ-ኦክሳይድ(Antioxidant) ስላለው ተመራማሪዎቹ ቡናን በየቀኑ መጠቀም ዘላቂ የጉበት ጠባሳ፣ ለረጅም ጊዜ የጉበት በሽታዎች ሊከሰት ከሚችለው ጉዳት፣የሰባ የጉበት በሽታ፣ የቫይረስ ሄፓታይተስ፣ ከአልኮል ጋር የተያያዘ የጉበት በሽታ እና ሌሎችንም ጨምሮ ቡና የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።
ሲርሆሲስ የተባለው የጉበት በሽታ በዓለም ዙሪያ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የሚያጠቃ የጉበት በሽታ ሲሆን በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ይገድላል። ሰዎች ቡናን በቀን አምስት ወይም ከዚያ በላይ ኩባያዎች ቢጠጡም እንኳ ዕለታዊ የቡና ኩባያዎ የጉበት በሽታ ወይም የጉበት ካንሰር የመያዝ እድልዎን ሊቀንስ እንደሚችል አዲሱ ጥናት አረጋግጧል።
እነዚህ ተመራማሪዎች 354,000 ናሙናዎችን/ሰዎችን) በመጠቀም ጥናቱን ከአስር አመታት በላይ ተከታትለውታል።
በዚህም የጥናቱ ውጤት ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በክሊኒካል ጋስትሮኢንተሮሎጂ እና ሄፓቶሎጂ መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን ይህ ጥናት ምናልባት የቡናን ተጽእኖ በተመለከተ “ለረጅም ጊዜ ክትትል የተደረገበት ጥሩ ጥናት ነው” ሲሉ በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲዳርስ-ሲናይ የሕክምና ማዕከል የሄፓቶሎጂ ንቅለ ተከላ ባለሙያ የሆኑት የመጀመሪያ የጥናቱ ደራሲ ዶ/ር ህዩንሶክ ኪም ተናግረዋል።
በጥናቱ መሠረት ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ የተባለው በጣም የተለመደው የጉበት ካንሰር ሲሆን በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 685,000 የሚጠጉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን ከ597,000 በላይ ሰዎችን በየአመቱ ለሞት ይዳርጋል። ተመራማሪዎቹ ቡናን አብዝቶ መጠጣት የጉበትን ጤንነት ይበልጥ ይጨምራል ብለዋል።
👉በቀን ከአንድ እስከ ሁለት ኩባያ የሚጠጡ ሰዎች:-
📌ለሲርሆሲስ የመጋለጥ እድላቸው በ 20% ይቀንሳል፣
📌ለጉበት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው በ 24% ይቀንሳል።
📌 በጉበት ምክንያት የመሞት እድልን በ31% ይቀንሳል።
👉በቀን ከሶስት እስከ አራት ኩባያዎች የሚጠጡ ሰዎች ደግሞ በሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር ተጋላጭነትን በ35% ይቀንሳል፣ ከጉበት ጋር በተያያዘ የመሞት እድልን በ41% ይቀንሳል።
👉አምስት ኩባያዎች ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች በሲርሆሲስ የመያዝ እድላቸው በ 32% ይቀንሳል፣ በጉበት ካንሰር የመያዝ አደጋን በ47% ይቀንሳል እና ከጉበት ጋር የተያያዘ ሞትን በ 42% እንደሚቀንስ ጥናቱ አረጋግጧል። ነገር ግን ቡናው በሚጠጣበት ጊዜ የስኳር መጠን እና የሚጨመሩ ሌሎች ማጣፈጫዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥናቱ መክሯል። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉት።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.