ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በአምስተኛው የኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ማጠናቀቂያ ለኢትዮጵያ የ464 ሚሊዮን ዶላር ተጨማ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በአምስተኛው የኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ማጠናቀቂያ ለኢትዮጵያ የ464 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር ክፍያ ፈቀደ
ይህም አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፉን 2.647 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል።
ድርጅቱ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የተመዘገቡትን የወጪ ንግድ እና የታክስ ገቢ እድገቶች ያደነቀ ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መናር ያሳደረውን ጫና ለመቋቋም 200 ሚሊዮን ዶላር ቀድሞ እንዲለቀቅ ማድረጉን ገልጿል።
​በተጨማሪም IMF ሁለተኛ ዙር የዋጋ ንረት ከተከሰተ ብሔራዊ ባንክ ፖሊሲውን ይበልጥ ሊያጠብቅ እንደሚገባ አሳስቧል።
ባንኩ በወርቅ ግብይት ላይ ያለውን ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያቆም፣ ድጎማዎች ሲነሱ ተጋላጭ ወገኖች እንዲጠበቁ፣ እና አዳዲስ ገለልተኛ የቦርድ አባላትን በመሾም የባንኩን ገለልተኝነት እንዲያጠናክር መክሯል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2