የኢንደስ ውኃ የጦርነት ስጋት ደቅኗል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በህንድና ፓኪስታን መካከል የሚገኘው የኢንደስ ውሃ አሁን ላይ ለሁለቱ ሀገራት የፖለቲካ መፋጠጥ ማዕከል ሆኗል።

በኒው ዴሊሂ እና እስላማባ መካከል በ1960 ተፈረሞ የቆየው የኢንደስ ውኃ ስምምነት አሁን አደጋ ላይ ወድቋል።

ሕንድ በ2025 በካሽሚር በነበረው ግጭት ምክንያት ስምምነቱን በጊዜያዊነት አግዳ ቆይታለች።

ፓኪስታን በበኩሏ የህንድ ድርጊት ሕገ ወጥ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ውኃን እንደ መሣሪያ መጠቀም የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብላለች።

የፓኪስታን የግብርና ዘርፍ 90 በመቶ የሚሆነው በኢንደስ ተፋሰስ ላይ ጥገኛ በመሆኑ ሕንድ ውኃውን የመቆጣጠር ዕቅድ በመግለጿ ፓኪስታን ስጋት እንዲገባት አድርጓል።

የሁለቱ ሀገራት የውኃ ሃላፊዎች ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመቋረጡ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ዕድሉ መጥበብን ነው የተገለፀው።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጡ እና እየተባባሰ የመጣው የቃላት ጦርነት ጉዳዩን ከውኃ ድርሻ አልፎ ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊቀይረው የሚችልበት ዕድል ይኖራል ሲል የፃፈው የህንዱ ኒው ዲልሂ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Indusriver #India #Pakistan
#NewDelhidaily


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2