📌የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልእክት አስተላለፈ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትረስት (Trust)፣ ጎግል ቲቪ (Google TV) እና ኖውን (Known) የተባሉ ጉዳት አምጪ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን በመግለጽ ለደንበኞቹ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።
እነዚህ አደገኛ መተግበሪያዎች በማስፈንጠሪያዎች (links) አማካይነት እንደ ጎግል ክሮም (Google Chrome)፣ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ባሉ መድረኮች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ሲሆን በስልክ ላይ ከተጫኑ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ የገንዘብ ዝውውር ሊያካሂዱና ሌላም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ባንኩ አሳስቧል።
ማኅበረሰቡ ራሱን ከዚህ ጥቃት እንዲጠብቅ ያስገነዘበው ባንኩ መተግበሪያዎችን ወደ ስልክ ለማውረድ እንደ ፕሌይ ስቶር (Play Store) ወይም አፕ ስቶር (App Store) ያሉ የታመኑ ምንጮችን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ አስታውቋል።
በተቃራኒው በጎግል ክሮም፣ በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ አማካይነት የሚላኩ መተግበሪያዎችን ፈጽሞ ወደ ስልክ አለማውረድ እና አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን ሳያረጋግጡ አለመክፈት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል። ከተጨማሪ ጥንቃቄዎች መካከልም በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ላይ የባዮሜትሪክ እና የፒን (PIN) የደኅንነት ማረጋገጫዎችን አጣምሮ መጠቀም ዋነኛው መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ማንኛውም አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥም በ951 የነጻ ስልክ መስመር ላይ በመደወል ፈጣን ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ባንኩ አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.