📌”ቢያንስ 21,000 ህፃናት ተገድለዋል” – ሴቭ ዘ ችልድረን
#Ethiopia | እስራኤል እና ሀማስ ግጭት ውስጥ ከገቡ 1000 ቀናት ተቆጥረዋል። ሁለቱ ወገኖች ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ከሁለት አመት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ነገርግን እስራኤል ስምምነቱን በመጣስ በፈፀመቻቸው ጥቃቶች የንፁሃን ህይወት ተቀጥፏል፣ የአካል እና ንብረት ጉዳት ደርሷል።
ሴቭ ዘ ችልድረን (Save the Children) ባወጣው ሪፖርት የጦርነቱ ገፈት ቀማሾ ህፃናት መሆናቸውን ጠቁሟል።
ቢያንስ 21,000 ህፃናት መገደላቸውን የተቋሙ አሀዛዊ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከ800,000 በላይ ወይም 80% የሚሆኑት የጋዛ ህፃናት ደግሞ ተፈናቅለዋል ተብሏል።
7,000 በላይ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው መለያየታቸው ተገልጿል።
ወደ 625,000 የሚደርሱ ለትምህርት የደረሱ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ለመራቅ ተገደዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተፈጸመበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 275 ህፃናት በእስራኤል ጦር መገደላቸውን አመላክቷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#savethechildren #Thiqah
Source: GetuTemesgen








No comments yet.