*ልብ የሚያሞቀው የሚሲ ሙገሳ ለቮዚና

- Advertisement -
Sidebar AD

*አንተ ታላቅ ተጫዋች ነህ ዜጎች በአንተ ሊኮሩ ይገባል

#Ethiopia | የካቦ ቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ ከአርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ጋር በሜዳ ላይ የነበረውን ስሜታዊ ገጠመኝ ተናግሯል።

ቮዚንሃ እንደገለጸው ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ሜሲ ወደ እሱ በመምጣት አንተ ታላቅ ተጫዋች ነህ ዜጎች በአንተ ሊኮሩ ይገባል በማለት እንዳደነቀው ገልጿል።

ይህ የሜሲ ድንቅ ንግግር ለቮዚንሃ ትልቅ ትርጉም ያለው እና በህይወቱ የማይረሳ ጊዜ እንደሆነ ገልጿል።

የካቦ ቨርዴው ግብ ጠባቂ በምላሹ ለሜሲ ምስጋናውን አቅርቦ “አንተ የሁላችንም ምልክት ነህ” ማለቱን ገልጿል።

ሜሲ ከጫወታው መጠናቀቅ በኋላ መልበሻ ክፍል በማምራት ለቮዚና ማለያውን የሰጠው ሲሆኔ ቮዚናም በታላቅ ደስታ ማለያውን ለሜሲ አበርክቷል።

ይህ ከእግርኳስ በላይ የሆነው ስሜት ብዙዎች እየተጋሩት ይገኛሉ።

ተሸንፈው የአለም ህዝብ ልብ ያሸነፉት ካፖ ቨርዴዎች የአለም ዋንጫ ታሪክ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Worldcup #Messivozinha
#Argentinacapeverde


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: