በአዊ ዞን በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ 7 ሰዎች ህይወታቸውን አጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባንጃ ወረዳ ዛሬ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ 7 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።

አደጋው ከቅዳማጃ ከተማ ወደ አስኩና ሲጓዝ የነበረ ባጃጅ ከሲኖትራክ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ሲሆን፣ በአደጋው የባጃጁ አሽከርካሪን ጨምሮ 7 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

የባንጃ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ በባጃጁ ውስጥ የነበረች አንዲት ሕጻን በሕይወት የተረፈች ሲሆን፣ ሁለት ተጎጂዎችም ለህክምና ወደ አቅራቢያ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከህይወታቸው ካለፉት መካከል 5 ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑ ተነግሯል።

የባንጃ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ጥልቅ ሀዘኑን በመግለጽ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናቱን ገልጿል።

ነፍስ ይማር።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: