ሦስት መንታ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በባላመር ከተማ ነዋሪና ታታሪ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት የአቶ ሳሙኤል ቡናይ ሦስት መንታ ልጆችን ነገ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በኦክሚ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ይመረቃል።

በአንድ ጊዜ ወደዚች ምድር የተቀላቀሉት ህፃን ይድነቃቸው፣ ሬድኤት እና ኬልሺ ሳሙኤል ለዚህ የትምህርት ማዕረግ መብቃታቸው፣ ከጀርባው የነበረውን የአባታቸውን እጅግ አድካሚና አርአያነት ያለው የሕይወት ትግል ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

​አቶ ሳሙኤል በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያት ልጃቸውን ለማሳደግ ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያላደረጉት ጥረት አልነበረም ፤ በተለይም የእናት ጡት ወተት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ተጨማሪ የህፃናት ወተትን በውድ ዋጋ በመግዛትና ሌት ተቀን በመልፋት ልጆቹን በጽናት አሳድጓል።

ከዚህም አልፎ የልጆቹ ዕድሜ ለትምህርት ሲደርስ በኦክሚ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ነገ ሀገርን የሚረከቡና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎችን ለማፍራት ላደረጉት የጀግንነት ጥረት ከፍተኛ አድናቆትና ዕውቅና ተችሯቸዋል ሲል በቅርብ የሚያውቀው ናትናኤል ተናግሯል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: