#Ethiopia | ነቢይ ግጥም ሲጽፍ ነው የኖረው፤ ግጥም ብቻ ግን አይደለም፣ ምርጥ ቲያትሮችንም ጽፏል፡፡ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈለት “ባለጉዳይ” የቴሌቪዥን ድራማውም አይረሳም፡፡ የትርጉም ሥራዎቹም ድንቅና ልዩ ናቸው፡፡
ነቢይ የብዕር ሰው ብቻ አልነበረም፤ ጨዋታው አፍ የሚያስከፍት አንደበተ ርቱዕም ነበረ እንጂ፡፡ ሰብአዊነት የተላበሰ፣ ደግና የፍቅር ሰው፣ የእውነትም ሰው ነበር።
ከነበረን ቅርበት የተነሳ ከለገሰኝ ወንድማዊ ምክሮቹ መካከል “ጭብጨባ ወዳለበት ሥፍራ አታዘወትር” የሚለው ሁሌም ከሕሊናዬ አይጠፋም፤ እጅጉን ጠቅሞኛልም። ጊዜ ተወስዶ በጥሞና የሚጻፉ ሌሎች ብዙ አይረሴ ቁምነገሮችንም ነግሮኛል፡፡
ግን ግን አሁንም ነፍሱ ከግጥም የምትለይ አይመስለኝም፡፡ ነፍሱና ግጥም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ እናም ሰማይ ቤት ሆኖም ግጥም እየጻፈ ያለ ይመስለኛል፤ ክፋቱ ግን እኛ አናነበውም፡፡ በሞት መለየቱ፣ ሌላው ቢቀር ብዙ ግጥሞችን አሳጥቶናል፡፡ ይሁንና የፈጣሪ ፈቃድ ነውና ነፍሱ በሰላም ትረፍ፡፡
ሁሌም አንረሳህም!
የሥራ ባልደረባህ


Source: GetuTemesgen









No comments yet.