የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የዜጎች ደህንነት መደፍረስ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መግለጫ፤ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሰብአዊ መብት አያያዙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል።
“የዜጎችን ህይወትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚመለከታቸው አካላት ቅድሚያ ሰጥተው ሊንቀሳቀሱ ይገባል” ሲልም አሳስቧል።
የጸጥታ መደፍረስ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በዜጎች እንቅስቃሴ እና በኑሮ ላይ እያደረሱ ያለው ጫና ከፍተኛ መሆኑንም መግለጫው ጠቁሟል።
ኢሰመኮ በተጨማሪም፤ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብሏል።
በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል ከመንግስት እና ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር በመተባበር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ኮሚሽኑ አረጋግጧል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.