#FastMereja I በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑት ቤተሰብ የተገኘው በአሁኑ ወቅት በካናዳ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ ውስጥ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ወጣቱ አማካይ አሊ አህመድ። ሁለቱም ወላጆቹ ከኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ሐረርጌ በዴሳ የተገኙት አሊ፣ በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ መድረክ ተስፋ ሰጪ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።
በእግር ኳስ ስፖርት ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና በአሁኑ ወቅት በሜዳ ላይ በሚያሳየው ቀልጣፋ እንቅስቃሴ ስሙ እየገነነ የመጣው አሊ አህመድ፣ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ገና በስድስት ዓመት ዕድሜው በሰሜን ቶሮንቶ የስፖርት ክለብ (North Toronto SC) እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። ከወላጆቹ ከአቶ አፈንዲ እና ከወይዘሮ ሙና የተወለደው አሊ፣ እንግሊዝኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን አቀናጅቶ መናገር የሚችል ሲሆን፣ ከእግር ኳስ በተጨማሪ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ከፍተኛ ፍላጎት አለው።
አሊ አህመድ በታዋቂዎቹ የእግር ኳስ ኮከቦች ሊዮኔል ሜሲ እና ኤደን ሀዛርድ እንዲሁም በእንግሊዙ ቼልሲ ክለብ አጫዋች ዘይቤ ተጽዕኖ አድሮበታል። በቅርጫት ኳስ በኩል ደግሞ እንደ ኮቢ ብራያንት፣ ዴማር ዴሮዛን እና ስቴፍ ካሪ ያሉ የኤንቢኤ (NBA) ታላላቅ ተጫዋቾችን በአርአያነት እንደሚከተል ይነገራል። ይህ የተለያየ የስፖርት ፍቅርና ክህሎት በሜዳ ላይ ላለው የአስተሳሰብ ብስለትና የአካል ብቃት ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተለት የስፖርት ተንታኞች ይገልጻሉ።
#ስፖርት ዘገባ
Source: FastMereja









No comments yet.