ሞሮኮ ካናዳን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ አለፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን “የአትላንቲክ አንበሶች” ካናዳን በማሸነፍ ወደ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በማለፍ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

ድሉ በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ትልቅ ኩራት በመሆን ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንና ከስፖርት ተንታኞች ሰፊ አድናቆት አግኝቷል።

በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሞሮኮ ቡድን ያሳየው የተደራጀ መከላከል፣ ጠንካራ የቡድን መንፈስ እና የታክቲክ ብልሃት በስፋት ተወድሷል።

በተጨማሪም በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተወለዱና ያደጉ ተጫዋቾችን በአንድ ዓላማ በማሰባሰብ የተፈጠረው ጠንካራ ቡድን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት መሆኑ ተጠቅሷል።

ታዋቂው የስፖርት ኮመንታተር ፒተር ድሩሪ የሞሮኮን የጨዋታ ስልት በማድነቅ፣ ቡድኑ በመጀመሪያው አጋማሽ ካናዳን ከባድ ጫና ውስጥ እንዳስገባ እና በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን በከፍተኛ ብልሃት እንደተቆጣጠረ ገልጿል።

ጋሪ ሌንከር በበኩሉ የሞሮኮ ወደ ሩብ ፍጻሜ መድረስ የአጋጣሚ ውጤት ሳይሆን የጥራትና የዝግጅት ውጤት መሆኑን ሲገልጽ፣ ይህ የአፍሪካ እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን ያሳያል ብሏል።

አላን ሺረርም የሞሮኮን የመከላከል አደረጃጀትና የተጫዋቾቹን መረጋጋት በማድነቅ፣ ቡድኑ የታክቲክ እግር ኳስ ምሳሌ መሆኑን ገልጿል።

ተንታኞች እንደሚሉት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፉት ዓመታት በስልጠና ማዕከላት፣ በዘመናዊ መሠረተ ልማት እና በተሰጥኦ ልማት ላይ ያደረገው ሥራ ዛሬ ፍሬውን በማሳየት ለአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ኩራት ሆኗል።

አለባቸው ደሳለኝ ( ከለንደን )


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2