#Ethiopia | የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዓለማቀፍ ቅርስ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት የላሊበላን ማኅበረሰብ “አባ ውዴ” ወይም “ሃሚና” በመባል ከሚታወቁና ቤት ለቤት እየዞሩ በዘፈን መልክ በልመና ከሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በማያያዝ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን አጥብቆ ኮነነ።
ጽሕፈት ቤቱ ድርጊቱን የፈጸሙትን “ለታሪክ ግድ የሌላቸውና ችኩል” ሲል የገለጻቸው ሲሆን ታሪካዊውን ስፍራ ከእንደዚህ ዓይነት አሳፋሪ ተግባር ጋር ማስተሳሰር የታሪክ መዛባትንና ፍልሰትን የሚያስከትል የድንቁርና ሥራ መሆኑን አሳስቧል።
በተለይም አንዳንድ አርቲስቶችና አዝማሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የስፍራውን ስም ያላግባብ እየተጠቀሙበት መሆኑን የጠቆመው መግለጫው በልመና የተሰማሩት እነዚህ ወገኖች ከላሊበላ አካባቢ ሕዝብ ባሕልም ሆነ ሥነ-ልቦና ጋር ምንም ዓይነት ቁርኝት እንደሌላቸው አስገንዝቧል መባሉን ዋዜማን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ይህ የስም ማጥፋትና የታሪክ መዛባት ድርጊት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን ያስታወሰው ጽሕፈት ቤቱ በድርጊቱ የተሰማሩ አካላት በአስቸኳይ ከስሕተታቸው ታርመው ለፈጸሙት የስም ማጠልሸት ተግባር ይቅርታ እንዲጠይቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ አቅርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.