ዜና

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ድል

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቶች በ2026 የፕሪፎንቴይን ክላሲክ ዩጂን ዳይመንድ ሊግ እና በ57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ላይ ድንቅ ውጤት በማስመዝገብ የአገራቸውን ስም አስጠርተዋል።

በዩጂን ዳይመንድ ሊግ የሴቶች የሁለት ማይል ውድድር አለሺኝ ባወቀ በ9:20.02 የወቅቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አንደኛ ስትሆን፣ ሒሩት መሸሻ በ9:20.20 ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ማርታ አለማየሁ 4ኛ፣ የኔዋ ንብረት 7ኛ እና አሳየች አይቼው 8ኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽመዋል።

በሴቶች የአንድ ማይል ውድድር ሳሮን በርሀ 11ኛ ሲሆን፣ ወርቅነሽ መሰለ 13ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል በአሜሪካ በተካሄደው 57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ በ31:02 አንደኛ ስትሆን፣ መልክናት ውዱ በ31:03 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የኢትዮጵያን የረጅም ርቀት ሩጫ የበላይነት አረጋግጠዋል።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: