በኢትዮጵያ የግሉን ሴክተርና የኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር ያለመ የንግድ ዎርክሾፕ ተካሄደ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I አሎሃ ቪስታ ኃ.የተ.የግ.ማ የመንግሥትና የግሉን ሴክተር ተዋናዮች፣ የዲፕሎማቲክ ኮር አባላትን እንዲሁም አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ያገናኘ ከፍተኛ የንግድ ለንግድ (B2B) ትስስርና የዎርክሾፕ መድረክ በዛሬዉ እለት በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።

ዝግጅቱ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት፣ የኢንቨስትመንት ማስፋፋት እና የግሉ ሴክተር ማጠናከር ላይ የሚሰሩ የመንግሥት ሚኒስትሮችን፣ የንግድ ምክር ቤቶችን፣ ባለሀብቶችንና የዘርፉን ባለሙያዎች በአንድ መድረክ ያሰባሰበ ነበር።

መርሀ-ግብሩ የመንግሥት አመራሮች በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በኢንቨስትመንት ፖሊሲና በንግድ አካባቢ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

መርሀ-ግብሩ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ሪል እስቴት፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በዘርፎቹ ያሉ የገበያ እድሎች፣ የኢንቨስትመንት አቅጣጫዎች እና ዋና ዋና ተግዳሮቶች በባለሙያዎች ቀርበው የፓናል ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የአሎሃ ቪስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄለና ንጉሳይ እንደገለፁት፤ “ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚገነባው በጠንካራ ሽርክና፣ በእውቀት ልውውጥ እና በተግባራዊ የንግድ ትስስር ነው”ካሉ በኋላ፣ አሎሃ ቪስታ በቀጣይም ተጨባጭ የንግድ እድሎችን የሚፈጥሩ መድረኮችን በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ወደፊት ጉዞ አስተዋጽኦ ማድረጉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በዕለቱ ከተደመጡት የክብሩ እንግዶች መካከል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸዉ አፍሪካ ከፖለቲካ ነፃነት ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ራሷን የመቻል ጉዞ ላይመሆኗን ጠቁመው፣ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በአግባቡ በመጠቀምና በመንግስትና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ቀጣይነት ያለው ውይይት በማድረግ ድህነትን ማሸነፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የመድረኩ ዋና አካል በነበረው የንግድ ለንግድ ትስስር ክፍለ-ጊዜ፣ ተሳታፊዎች በቀጥታ በመገናኘት አዳዲስ የንግድ እድሎችን መለዋወጣቸውና ለወደፊት የሚሆኑ ስልታዊ ሽርክናዎችን መመሥረታቸው ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1