የሀዋሳው የቅዱስ ገብርኤል በዓል በድምቀት ተከበረ፤ ከንቲባው ለእንግዶች ጥሪ አቀረቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በሀዋሳ ከተማ የዘንድሮው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በከፍተኛ ድምቀት፣ በሰላምና በተዋበ ሥነ ሥርዓት መከበሩን የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ።

ከንቲባ ጥራቱ በየነ ለበዓሉ የታደሙትን ምዕመናንና እንግዶች እንኳን አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን፣ ከሩቅና ከቅርብ የመጡ በርካታ እንግዶች በከተማዋ መገኘታቸው ለበዓሉ ልዩ ድምቀት መስጠቱን ገልጸዋል።

ከንቲባው አክለውም እንግዶች በዓሉ ካበቃ በኋላም ቢሆን ቆይታቸውን በማራዘም የሀዋሳ ሐይቅን፣ የከተማዋን ንጹሕ አየርና የሕዝቡን እንግዳ ተቀባይነት እየተለማመዱ መልካም ጊዜ እንዲያሳልፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም በዓሉ በሰላምና በውበት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ የመንግሥት አመራሮች፣ ባለሀብቶች፣ የሆቴል ባለቤቶች፣ በጎ ፈቃደኞችና የመላው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የከበረ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: