የነጻ ምሳ የሚበላበት ሬስቶራንት
#Ethiopia |የሆሊውዱ ኮከከብ የዊል ስሚዝ ሁለተኛ ልጅ ድምጻዊና ተዋናይ ጄደን ስሚዝ የራሱን ገቢ ማሳደጊያ የሚሆን ውድ የከበርቴዎች ምግብ ቤት ከመክፈት ይልቅ ቤት አልባዎች በነፃ የሚመገቡበት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመስረት ለጎዳና ተዳዳሪዎች አርአያነት ያለው ደግነት እያሳየ ይገኛል።
እ.ኤ.አ. በ2019 “አይ ላቭ ዩ” (I Love You) በሚል ስያሜ በተንቀሳቃሽ የምግብ መኪና የተጀመረው ይህ ጥረት በሎስ አንጀለስ በሚገኘው ‘ስኪድ ሮው’ ለሚኖሩ ቤት አልባዎች ነፃ የእፅዋት ተወፅኦ ምግቦችን በማቅረብ ስራውን ጀምሯል።
ይህ በጎ አድራጎት በአሁኑ ወቅት አቅሙን በማሳደግ ትኩስ ምግቦችን፣ የታሸጉ ውሃዎችንና የተለገሱ አልባሳትን ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያቀርብ ተቋም ሆኗል።
በአንዳንድ አጋጣሚዎች በአንድ መርሃ-ግብር ብቻ እስከ 500 የሚደርሱ ነፃ ምግቦችን የሚያከፋፍለው ይህ ድርጅት በቀጣይም በዚሁ አካባቢ ቋሚ ህንፃ በመገንባት በየቀኑ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በነፃ ለማቅረብ እንዲሁም የስራ እድልና አዎንታዊ የማህበረሰብ መኖሪያ ቦታ ለመፍጠር አልሞ እየሰራ ይገኛል።
የዚህ ወደፊት የሚገነባው ምግብ ቤት አሰራር አቅም የሌላቸው ወገኖች በነፃ እንዲመገቡ የሚያደርግ ሲሆን የገንዘብ አቅም ያላቸው ደንበኞች ደግሞ የሌሎችን ምግብ የሚሸፍን ክፍያ እንዲከፍሉ በሚያስችል የመረዳዳት መርህ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ያደርጋል።
ጄደን ስሚዝ ይህንን ተቋም “አይ ላቭ ዩ” ብሎ የሰየመበት ዋና ምክንያት ”ፍቅር በቃል የሚነገር መፈክር ብቻ ሳይሆን በተግባር የሌላውን ሰው ረሃብ በማስወገድ የሚገለጽ እውነተኛ ሰብአዊነት በመሆኑ ነው” ብሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.