ሄፓታይተስ ቢ የመተላለፍ እድሉ ከኤች.አይ.ቪ (HIV) ጋር ሲነጻጸር በ30 እጥፍ ይበልጣል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር አስናቀ አበበ እንደሚያስረዱት፤ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በግብረ-ስጋ ግንኙነትና ወቅት የመተላለፍ እድሉ ከኤች.አይ.ቪ (HIV) ጋር ሲነጻጸር እስከ 30 እጥፍ ይበልጣል።

በሀገራችን ከ9 እስከ 10 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በዚህ ቫይረስ እንደሚያጠቃ መረጃዎች ያሳያሉ።

​ስለሆነም ራሳችንንና ወዳጆቻችንን ከዚህ በሽታ ለመጠበቅ እንዲሁም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸው ዋና ዋና የምክር ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

​1. ቅድመ-ጥንቃቄና መከላከያ መንገዶች
​የጥንቃቄ አሰራርን መከተል፦

ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ እንደመሆኑ ልክ ለኤች.አይ.ቪ እንደሚደረገው ሁሉ በግብረ-ስጋ ግንኙነት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እና በደም የተበከሉ ስለታም ቁሳቁሶችን ከሌሎች ጋር አለመጋራት ያስፈልጋል።

​ሄፓታይተስ ቢ ክትባት መከተብ፦ በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ የሌለባቸው ሰዎች ቀድመው የሄፐታይቲስ ቢ ክትባትን በመውሰድ ሙሉ በሙሉ መከላከል ይችላሉ።

​2. የበሽታውን ምልክቶች በጥንቃቄ መከታተል

​የበሽታው ምልክቶች በሁለት ተከፍለው ይታያሉ፡

*​በአጭር ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች፦

የሰውነት ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ፣ የቆዳና የዓይን ቢጫ መሆን።

*​በረጅም ጊዜ (Chronic – ከ6 ወር በላይ) የሚታዩ ምልክቶች፦

የሰውነት ድካምና ማበጥ፣ ደም ማስታወክ፣ የመንገዳገድ ስሜት እና የሰገራ መጥቁር።

​3. ለተያዙ ሰዎች የሚሰጥ የህክምና ምክር
​ቋሚ የህክምና ክትትል፦

ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜ (ከስድስት ወር በላይ) የሚገኝባቸው ሰዎች (Chronic Hepatitis) ቫይረሱ ጉበት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ቋሚ የህክምና ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል።

​በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2