የ13 እና የ18 ዓመት ሴት ልጆችን የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
ከ18 ዓመት በታች የሆኑትን ልጃገረዶች የግብረ ስጋ ግንኙነትና እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡
ተከሳሽ ወርቁ ሻመና ዕድሜያቸው 13 እና 18 አመት በሆኑ ሁለት ህፃናት ላይ መስከረም 20/2018 ከምሸቱ 5 ሰአት ገደማ በዚሁ ዲላ ከተማ ሀሮሬሣ ቀበሌ በደቻ ቀጠና ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ ህፃን ትዕግሥት ዮሴፍ ከአሳዳጊዎች ቤት ጠፍታ ወደ አንዲዳ አከባቢ ከቤት ሰራተኛ ከሆነችው 2ኛ ተበዳይ ጋር እየሄደች እያለ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አከባቢ ተከሳሹ አግኝቶ ” ጊዜው መሽቷል !! ጅብ ይበላችኋል!! ” ብሎ ወደ ቀበሌ ወስጄ ቀጠና አሳድራችሃለሁ በማለት ወስዶ በአንድ ቤት ውስጥ ካስገባ ቦሃላ በመጀመሪያ ተበዳይ በሆነችሁ በህፃን ትዕግስት ዮሴፍ (13) ዓመቷ ላይ የወንጀል ጥቃት አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኙናት ሲሞክር ህፃኗ ያለ የሌለ አቅም በመጠቀም ራሷን ተከላከላለች።
ይህቺንማ አልችላትም !! በማለት ወደ ሁለተኛዋ ህፃን ኢየሩሳሌም ዕድሜ 18 የሆነችውን ይሄዳል እሷን ሌሊቱን ሙሉ በተደጋጋሚ ጥቃት በመድረስ ክፉኛ ጓድቷታል በዚህም አስገድዶ የግብረስጋ ግንኙነት በማድረግ ወንጀል መፈፀሙን አቃቤ ህግ ባቀረበው ማስረጃ አስረግጦ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱን የችልቱ ዳኛ አቶ አብርሃም ኡዶ ገልፀዋል።
የዲላ ከተማ አቃቤ ህግ የሆኑት ወ/ሮ ዝናሽ ማሞ በተከሳሽ ላይ የክስ ማክበጃ ሀሳብ በአንቀፅ ጠቅሰው ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የአቃቤ ህግ እና የተከሳሽ የክስ ማቅለያን በደንብ መርምሮ ተከሳሽ የመንግስት ሰራተኛና የህዝብ አገልጋይ እንዲሁም የ9 ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የለሌበት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት አስተማሪ ሊሆን ይችላል የሚል የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።
በዚሁ መነሻ ፍ/ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 149/1 ድንጋጌ መሰረት በተከሳሽ ወርቁ ሻመና ላይ የ5 አመት ፅኑ እስራት ማሳለፉን የዲላ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Yeneta Tube









No comments yet.