#ቦንጋ | በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ሸዳ ቀበሌ ውስጥ ባለሁለት እግር ሞተር ከአይሱዚ ጭነት መኪና ጋር በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።
በአደጋው የሞተር ሳይክሉ አሽከርካሪ እና ከኋላው ተሳፋሪ ሆኖ የነበረው ግለሰብ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የቢጣ ወረዳ ፖሊስ የትራፊክ አስተባባሪን ጠቅሶ የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በትራፊክ ፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን በበኩሉ፣ ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች የአደጋ መከላከያ ሄልሜት መጠቀም በአደጋ ጊዜ የጭንቅላት ጉዳትን ለመቀነስ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በድጋሚ አሳስቧል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.