#Ethiopia | ”በብር” ስም አወጣጥ ዙሪያ እንዲህና እና እንዲያ የሚባሉ በርካታ መላምንቶች ያሉ ቢሆንም ”ብርርርር” የማለቷ ነገር ግን ”ብር” አስብሏታል የሚለው ሚዛን ይደፋል።
ለመያዝ ታስቸግራለች ፤ ብርር ትላለች።የተቋማት የደም ስር ናት።ተቋማት በሁሉ ረገድ ልንቀሳቀስ ያሉ እንደሆን ዋናው ዋናዋ ቁም ነገር እርሷ ናት።
ሆኖም በተለይ በተቋማት ”ብሪቱ” በጥሬዋም ሀብት ፈጥራም ቢሆን አያያዝ አና ኦዲት ትሻለች።
ያለዛማ ሁሉ ዚመንዝራት እንዲሁ መብረሯ አይቀርምና ሙያን መሠረት ያደረገ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ስርአት በእጅጉ ያስፈልገናል።
ስለሆነም ፤ በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2014 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 332/2015 መሠረት በሕግ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE)፣ የሕዝብን ጥቅም ማስጠበቅን ዋነኛ ዓላማው አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ቦርዱ የዘርፉን አሰራር በመቆጣጠር ረገድ የጎላ ሚና ያለው ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና ዕውቅና ያለውን ብሔራዊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ከፍተኛ ኃላፊነትም ተጥሎበታል።
ተቋሙ ይህንን ዓላማውን ለማሳካት የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ደረጃዎችን ከመደነገጉም በላይ የባለሙያዎችን አሰራርና ሥነ-ምግባር የሚመሩ ደንቦችን ያወጣል።
በተጨማሪም በዘርፉ የሚሰማሩ ሙያተኞችንና ድርጅቶችን መዝግቦ የብቃት ማረጋገጫ የመስጠት የሙያ ማሻሻያና ቀጣይነት ያላቸው የሥልጠና ፕሮግራሞችን የማመቻቸት እንዲሁም የሕጉን የበላይነት በማስከበር መመሪያዎችን እና ደንቦችን በማይከተሉ አካላት ላይ ሕጋዊና የዲሲፕሊን እርምጃዎችን የመውሰድ ሰፊ ተግባራትን ያከናውናል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.