በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ70 ሺህ በላይ ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

*እነዚህ ቁጥሮች ተራ አኃዞች አይደሉም ህልምና ተስፋ የነበራቸው የሰው ልጆች ስም እንጂ!

#Ethiopia | የተሻለ ህይወት ፍለጋ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት በጉዞ ላይ እያሉ ህይወታቸውን የሚያጡ ስደተኞች ቁጥር አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ባለፉት 10 ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ግጭቶች የምጣኔ ሀብት ቀውስ እና የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ስደትን ምርጫቸው ያደረጉ ከ70 ሺህ በላይ ዜጎች መሞታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የገለፀው።

በ10 ዓመታት ውስጥ ማለትም ከፈረንጆቹ 2014 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው ይህን ቁጥር የተመዘገበው።

በአስር ዓመታት ውስጥ ከተመዘገበው የሞት መጠን ከግማሽ በላይ የሚሆነው በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የተከሰተ ነው ብሏል።

ከሰሜን አፍሪካ ወደ አውሮፓ ለማቋረጥ በሚደረጉ አደገኛ የጀልባ ጉዞዎች ከ30 ሺህ በላይ ስደተኞች በባህር ውስጥ ሰጥመው ህይወታቸውን ማጣታቸውን ድርጅቱ ገልጿል።

የIOM ሪፖርት እንዳመላክተው ህይወታቸውን ካጡ ስደተኞች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ማንነታቸው ወይም የመጡባቸው ሀገራት አይታወቅም ብሏል።

ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በስደት ምክንያት ወጥተው የቀሩ ቤተሰቦቻቸውን እጣ ፈንታ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሳያውቁ እንዲቀሩና ዘላቂ የስነ ልቦና ስቃይ ውስጥ እንዲወድቁ አድርጓል ብሏል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሀገራት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከል ባሻገር ስደተኞች ህጋዊና አስተማማኝ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሱበትን ስርአት እንዲዘረጉ ጠይቀዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#IOM #SearchRescue
#MissingMigrantsProject


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2