ሮናልዶ እናት ክለቡን ለመቅጣት ተነስቷል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ክርስቲያኖ ሮናልዶ የማንችስተር ዩናይትዱን ብሩኖ ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ናስርን እንዲቀላቀል የማሳመን ስራ እየሰራ መሆኑ ተነገረ።

ሮናልዶ ቡርኖን ለማሳመን ከፍተኛ እና ተከታታይ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተዘገበው።

የማንቸስተር ዩናይት የአማካይ ክፍል አንቀሳቃሽ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዝውውር መስኮቱ ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄዎች የሚቀርቡለት ቢሆንም ባለፈው የዝውውር መስኮት የወደፊት እጣ ፈንታውን ክለቡ እንዲወስን አድርጎ ነበር።

በወቅቱ በኦልድ ትራፎርድ የመቆየት ፍላጎት የነበረው ቢሆንም ክለቡ እሱን ለመሸጥ ከፈለገ ግን ለመልቀቅ ዝግጁ እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን ማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ላለመሸጥ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ፈርናንዴዝ በክለቡ የተጣለበትን እምነት በብቃት መልሷል።

በውድድር ዘመኑ 21 ግቦችን አመቻችቶ በማሲያዝ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአንድ ውድድር ዘመን ከፍተኛ የጎል አሲስት (Assist) ታሪክን በስሙ ማስመዝገብ ችሏል።

አሁን ላይ ደግሞ ሮናልዶ የቀድሞ የቡድን አጋሩን ወደ ሳውዲ ፕሮ ሊግ ለመውሰድ የሚያደርገው ጥረት በዝውውር መስኮቱ ከሚጠበቁት የዝውውር ወሬዎች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Manchesterunited
#Cristianoronaldo
#Burunoferenandez


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: