#Ethiopia | በታሪክ ውስጥ በርካታ እጅግ አስገራሚ ልብ የሚነኩ እና ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲጠቀሱ የኖሩ የፍቅር ደብዳቤዎች አሉ።
ነገር ግን በብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ በታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚው እና ጥበብ የተሞላበት የፍቅር ደብዳቤ ተብሎ የሚጠቀሰው የታዋቂው ሙዚቀኛ ሉድቪንግ ቫን ቤትሆቨን በፈረንጆቹ 1812 የተጻፈው ደብዳቤ ነው።
ይህ ደብዳቤ በታሪክ ውስጥ ለዘላለም ፍቅሬ በመባል ይታወቃል።
ቤትሆቨን ይህን አጭርና እጅግ ጥልቅ ደብዳቤ የጻፈው በፈረንጆቹ 1812 ሲሆን ደብዳቤው በሕይወት እያለ አልተላከም።
ደብዳቤው ከሞተ በኋላ በግል ሰነዶቹ መካከል ተደብቆ ነው የተገኘው።
ቤትሆቨን ደብዳቤውን የጻፈላት ሴት ማን እንደነበረች እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ አይታወቅም።
ይህም ደብዳቤውን የበለጠ አስገራሚና ምስጢራዊ አድርጎታል።
ይህ የፍቅር ደብዳቤ እንዲህ ይላል..
መልአኬ፣ ሕይወቴ፣ በአንቺ ፍቅር የተሞሉ የእንባ ዘለላዎች ወደ አንቺ ይፈሳሉ… አዎ፣ እወድሻለሁ፤ ካንቺ ውጪ ሌላ ማንንም ማፍቀር አልችልም።
ሁሌም የእኔ ሁኚ፤ እኔም ሁሌም የአንቺ ነኝ… እኛም የአምላክ ነን።
ሁልጊዜም የአንቺ ሁልጊዜም የእኔ ሁልጌዜም የእኛ…
የሚል ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#LudwigvanBeethoven
#TotheImmortalBeloved
Source: GetuTemesgen









No comments yet.