የቀድሞው የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት ተቀጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቀድሞው የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ በሕግ መጣስና ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል ጥፋተኛ በመባላቸው የእስራት እና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነባቸው።

በሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ በቀረበው ክስ መሠረት፣ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በመመርመር ተከሳሾቹ ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም «የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ)» በተባለ ታጣቂ ቡድን ማደራጀትና ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸው መረጋገጡን ገልጿል።

በዚህ መሠረት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስን በ10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እና በ4,000 ብር መቀጮ፣ አቶ ሽመልስ ቶማስን ደግሞ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በ1,000 ብር መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2