አንጋፋው ደራሲ አዲስ መጽሐፍ ይዞ መጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የተወዳጁ ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ አዲስ መጽሐፍ «የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ» ለንባብ መብቃቱ ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት አዲሱ መጽሐፍ በሁሉም የመጽሐፍ መደብሮች ውስጥ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንጋፋው ደራሲ ይህንን አዲስ ሥራውን ለአንባቢያን ሲያደርስ፣ በኪነ-ጥበብ ጉዞው በርካታ አጓጊ እና ተወዳጅ መጻሕፍትን ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ አበርክቷል።

ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ከዚህ ቀደም በሐመር ሕዝብ ባህልና አኗኗር ላይ ያተኮሩትን እንደ «ከቡስካ በስተጀርባ» (የበኩር ድርሰቱ)፣ «ኢቫንጋዲ» እና «የዘርሲዎች ፍቅር» የመሳሰሉ እጅግ ተወዳጅ ኤትኖግራፊክ ልብወለዶችን ለአንባቢያን አድርሷል።

ከዚህም በተጨማሪ «አቻሜ»፣ «የንሥር ዐይን»፣ እንዲሁም የጀግናውን የአርበኛ ጃገማ ኬሎን ታሪክ የሚያወሳው «ጃገማ ኬሎ – የበጋው መብረቅ» እና «የሚሳም ተራራ» የተሰኙ ድንቅ መጻሕፍቱ ይታወሳሉ።

አሁን ደግሞ ይህንን አዲስ «የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ» የተሰኘ መጽሐፉን በመጨመር የንባብ ማዕዶቱን አስፍቷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#newbook #amharicbook #fikremarkosdesta


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: