#Ethiopia | ከሁሉ በፊት የኢ-ቪዛ አገልግሎት ምንድን ነው?
ኢ-ቪዛ አንድ መንገደኛ ወደ ሌላ ሀገር ለመጓዝ የሚያስፈልገውን የመግቢያ ፈቃድ (ቪዛ) በኤምባሲዎች ወይም በቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች በአካል ሳይገኝ ሙሉ በሙሉ በበይነመረብ አማካኝነት የሚያመላክትበትና የሚቀበልበት ዘመናዊ አሠራር ነው።
አመልካቾች አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን በኦንላይን በመስጠትና ክፍያቸውን በመፈጸም የተፈቀደውን የቪዛ ሰነድ በኢሜይላቸው ይቀበላሉ።
ይህም አላስፈላጊ ውጣ ውረድንና የጊዜ ብክነትን በማስቀረት የጉዞ ሂደቱን እጅግ ፈጣን እና ቀላል ያደርገዋል።
በዚህ መሠረት ኢትዮጵያውያን ዜጎች በቀላሉ ወደ ሩሲያ መግባት የሚያስችላቸውን የኢ-ቪዛ አገልግሎት የሚያገኙበት አሠራር በቅርቡ ይፋ ሊደረግ መሆኑን ከሩስያው የዜና አውታር ስፑትኒክ ሰምተናል።
የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ፣ ለኢትዮጵያ፣ ለታንዛኒያ እና ለግብፅ ዜጎች የኢ-ቪዛ አገልግሎት መስጠት የሚቻልበትን እድል እያጠና እንደሚገኘ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ አክሎም ይህንን የኢ-ቪዛ ማመልከቻ እድል ከማስፋፋት ባለፈ ለበርካታ ጊዜያት መግባት የሚያስችለውን የኢ-ቪዛ አማራጭ ለማስተዋወቅ ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጥምረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጻል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.