* በትራምፕ ሊሸለም ነው!
#Ethiopia | በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘው የሴንታ ክሩዝ ሲብራይት (Seabright) የባህር ዳርቻ የ16 ዓመቱ ታዳጊ ላይፍጋርድ ራይደር ዊሊያምስ በኃይለኛ ማዕበል ተወስዶ ለሞት የተጋለጠን የ10 ዓመት ህጻን በጀግንነት በማዳኑ በመላው አሜሪካ ትልቅ አድናቆት እያገኘ ነው።
በምስክሮች በተቀረጸው ቪዲዮ መሠረት፣ ህጻኑ በድንገት በተነሳ ኃይለኛ ማዕበል ወደ ባህሩ ከተወሰደ በኋላ ራይደር ሳይዘገይ ወደ ውሃው ዘልቆ በመግባት ህጻኑን አጥብቆ ይዞ ከተደጋጋሚ ከባድ ማዕበሎች ጋር በመታገል እስከ ዳርቻ ድረስ ማድረስ ችሏል። በኋላም ሌላ ላይፍጋርድ በመድረስ ህጻኑ በደህና ወደ ዳርቻ ተወስዶ በሕክምና ከታየ በኋላ ለወላጆቹ ተሰጥቷል።
የማዳኑ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ሚሊዮኖች ተመልካቾች ታዳጊውን “እውነተኛ ጀግና” በማለት ሲያወድሱት ታይቷል።
አባቱም ልጁ ከልጅነቱ ጀምሮ በውሃ ስፖርቶችና በላይፍጋርድ ስልጠና የተዘጋጀ መሆኑን ገልጾ፣ “ልጁን ፈጽሞ አልለቀቀውም” ብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልእክት፣ ራይደርንና ቤተሰቡን እንዲሁም ያዳነውን ህጻን ወደ ነጩ ቤት በመጋበዝ ለታዳጊው “High Civilian Honor” የተባለውን ከፍተኛ የሲቪል ክብር ሽልማት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል።
ራይደር ዊሊያምስ በበኩሉ፣ ይህ በቪዲዮ የተቀረጸው ማዳን ብቻ ሳይሆን በዚያው ቀን ከስራ በኋላ ሌሎች ሁለት ሰዎችንም ከአደገኛ ማዕበል ማዳኑን ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews #America #Lifeguard #RyderWilliams
Source: GetuTemesgen









No comments yet.