🚨በየ5 ደቂቃው ምስል የሚያነሳውና ሰላይ የሆነው የስማርት ፎን ምስጢር ይፋ ሆነ‼️ከሰሜን ኮሪያ በምስጢር ተሰርቆ የወጣ አንድ የስማርት ፎን ስልክ፣ የመንግስቱ አገዛዝ የዜጎቹን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ምን ያህል በአስፈሪ ሁኔታ እንደሚቆጣጠር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርጓል።
ቢቢሲ (BBC) በሴኡል ካለው ዴይሊ ኤንኬ (Daily NK) ከተሰኘው የመገናኛ ብዙሃን ተቀብሎ ባደረገው የቴክኒክ ምርመራ፣ ስልኩ ከተራ መገናኛ መሳሪያነት ይልቅ በኪስ የሚያዝ የወታደራዊ የሰላይ መሳሪያ ሆኖ የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ ስልክ ተጠቃሚው የሚያደርገውን ማናቸውንም እንቅስቃሴ በየ5 ደቂቃው በምስጢር ፎቶ (Screenshot) በማንሳት ተጠቃሚው ሊከፍተው ወደማይችለው የተደበቀ ፎልደር ይልካል፤ ይህም መረጃ በመንግስት የደህንነት አካላት ብቻ የሚከፈትና ለቁጥጥር የሚያገለግል ነው።
በተጨማሪም ስልኩ ከማንኛውም የዓለም አቀፍ ኢንተርኔት አውታረ መረብ ጋር በፍፁም እንዳይገናኝ ተደርጎ የተዘጋ በመሆኑ ከውጭ ዓለም የሚመጣ ማናቸውንም መረጃ ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
ከዚህም በላይ ተጠቃሚዎች በሚጽፉበት ወቅት ስልኩ በራሱ የቃላት ማረምያ ስልቶችን በመጠቀም ቃላትን ይለውጣል። ለምሳሌ “ኦፓ” (Oppa – በደቡብ ኮሪያ ወንድምን ወይም ፍቅረኛን ለመጠራት የሚያገለግል ቃል) የሚለውን ወደ “ኮምሬድ” (Comrade – ጓድ)፣ እንዲሁም “ደቡብ ኮሪያ” የሚለውን ቃል ወደ “ተላላኪ ሀገር” (Puppet state) በማለት በራሱ ጊዜ አድሶ ይጽፋል።
ይህ መሳሪያ ስልክ ከመሆን ይልቅ የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ዜጎቹ ምን ማንበብ፣ ማወቅ፣ መጻፍ እና መናገር እንዳለባቸው ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የፈጠረው ዘመናዊ የኪስ ውስጥ የክትትልና የቁጥጥር መሳሪያ ነው ተብሏል።
@Seledadotio

No comments yet.