ኮሎምቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

የኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት አቤላርዶ ደ ላ ኤስፕሪኤላ ሀገራቸው ከምትከተለው አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ አካባቢዎች የሚገኙ 14 ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዳቸውን አስታወቁ።

ይህ ውሳኔ የኮሎምቢያን የዲፕሎማሲ ወጪዎች ለመቀነስ እና የተረፈውን በጀት እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ጸጥታ እና መሠረተ ልማት ባሉ የሀገር ውስጥ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለማዋል ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በዕቅዱ መሠረት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ፣ ጋና እና ሴኔጋል የሚገኙ ኤምባሲዎች የሚዘጉ ሲሆን፣ በነዚህ ሀገራት የሚገኙ የኮሎምቢያ ዜጎች በአቅራቢያ በሚገኙ ሌሎች ተወካይ መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።

በተጨማሪም የኮሎምቢያው መጪ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር የተለየ አካሄድ በመከተል ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ፣ የሀገሪቱን ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር እና የንግድና ጸጥታ ትብብሮችን ለማጠናከር ማቀዱ ታውቋል። አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ይህ የዲፕሎማሲ መዋቅር ማሻሻያ በስልጣን ቆይታቸው የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚገመገም ጠቁመዋል።

Via capital



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You Might like