ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2025 አመት ላይ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች የጉበት በሽታ እንዳለባቸው ሳያውቁ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ የጣለውና ዝምተኛ ገዳይ በመባል የሚጠራው የሄፓታይቲስ የጉበት በሽታ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ የአለም ጤና ድርጅት ተናግሯል።

የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት 287 ሚሊዮን የሚሆን የዓለም ሕዝብ በከባድ የሄፓታይቲስ “ቢ” እና “ሲ” ቫይረሶች ተይዞ ይገኛል ብሏል።

ሆኖም ግን ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ መኖሩን እንኳ እንደማያውቁ ነው የገለፀው።

በሽታው አስቀድሞ መከላከልና መታከም እንዲሁም ሙሉ በሙሉ መዳን የሚችል ቢሆንም ባለፈው ዓመት ብቻ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በዚሁ በሽታ ምክንያት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በፈረንጆቹ 2024 በአለም ዙርያ ከተወለዱ ህፃናት መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው በተወለዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ የመጀመሪያ የሄፓታይቲስ “ቢ” ክትባት ያገኙት ቀሪዎቹ አላገኙም ብሏል።

የአለም ጤና ድርጅት በየአመቱ ሃምሌ 21 ቀን የሚያከብረው ዓለም አቀፍ የጉበት በሽታ ቀን በነገው እለት እንደሚከበር ገልጿል።

አዲስ የሚወለዱ ሕፃናት በተወለዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ የመጀመርያ ደረጃ ክትባት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልጋ ድርጅቱ አስታውቋል።

ማንኛውም ሰው ቀደም ብሎ በሽታው ተመርምሮ የማያውቅ ከሆነ ወይም ለአደጋው ተጋላጭ ከሆነ አሁኑኑ የሄፓታይቲስ “ቢ” እና “ሲ” ምርመራ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#WHO
#WorldHepatitisday
#Vaccine


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: