ነገ በተለያዩ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነገ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የታቀደ የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲል በበርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና የክልል አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት እንደሚያቋርጥ አስታወቀ።

​ተቋሙ ባወጣው መረጃ መሠረት በጥገናው ምክንያት ከአዲስ አበባ ዋና ዋና የንግድና የመኖሪያ መንደሮች እስከ ክልል ከተሞች ድረስ በተለያየ የሰዓት ሰሌዳ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥ ይሆናል።

በዚህም መሠረት እንደ ስካይላይት ሆቴል፣ ኤድናሞል፣ ቦሌ ቴሌ፣ ቃሊቲ፣ ሳሚ ካፌ፣ አውጉስታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ እና ዱከም ባሉ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ደረጃ እንደ ጭሮ ከተማ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ፣ ጨላንቆ እና ቆቦ ባሉ አካባቢዎች ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የሰዓት ክፍተቶች እስከ አምሽቱ 11፡04 ድረስ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትዕግሥት እንዲጠብቁ በትህትና ጠይቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2