”አምታታው በከተማ”

- Advertisement -
Sidebar AD

ግብፅ ፌዴሬሽን

#Ethiopia | የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የግብፅ የሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾቹ በማልያቸው ላይ ያሳረፉት የሰባት ከዋክብት ነገር የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ቡድኑ በታሪኩ አህጉራዊውን ዋንጫ አንስቶ የማያውቅ በመሆኑ የከዋክብቱ መኖር በርካታ ሰዎችን “ሴቶቹ የተደበቀ የዋንጫ ታሪክ ይኖራቸው ይሆን?” በሚል ጥያቄና ግራ መጋባት ውስጥ ጥሏቸው ነበር።

​ሆኖም የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዚህ ምስጢር መልስ የሚያያዘው ከግብፅ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ጋር ነው የሚል አስቂኝ ምላሽ ሰጥቷል።

ፌዴሬሽኑ በእውኑ ሴቶች ወንዶች ናቸውን የሚለው ጥያቄ ግን ወደ ጎን የተወው ይመስላል።

ማልያው ላይ ያረፉት ሰባት ከዋክብት የሴቶቹ ቡድን ያሸነፋቸውን ዋንጫዎች ሳይሆን ከግብፅ የወንዶች ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ጋር የሚያያዝ ነው።

የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እነዚህን ከዋክብት የጠቅላላ ሀገሪቷ የእግር ኳስ ስኬት መግለጫ አድርጎ በመውሰዱ በሁሉም ብሔራዊ ቡድኖቹ ማልያ ላይ የሰባቱን ከዋክብት ምልክት እንዲያርፍ ወስኗል ነው የተባለው።

​የግብፅ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን እስካሁን በመድረኩ የመጨረሻዎቹ የዋንጫ ደረጃዎች ላይ ደርሶ የማያውቅ ቢሆንም ሴቶቹ ተጫዋቾች ደረት ላይ ከዋክብቱ እንዲሰቅሉ ግድ ሆኖባቸዋል።

በዚህ ወር ፍጻሜውን ባገኘው 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ በሞሃመድ ሳላህ የሚመራው የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድንም ተመሳሳይ ከዋክብት በደረታቸው ላይ አድርገው የነበረ ሲሆን ፊፋ ይሄን ኮከብ ቀዳችሁ ጣሉት ሲል ቀጭን ትዕዛዝ እንደሰጣቸው ይታወሳል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: