በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የገዛ እህቱን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በረከት ስዩም የተባለ ሲሆን በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ወካ አራባ ቀበሌ በ”ቡታ” ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በሚገኘው መኖሪያ ቤት የግል ተበዳይ የሆነችውን እህቱን ረድኤት ስዩም ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን ተገልጿል።
ከድርጊቱ በኋላ ለጊምቦ ወረዳ ፖሊስ ጥቆማ በመቅረቡ ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ጉዳዩን አጣርቶ ለጊምቦ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ያስተላልፏል።
ዐቃቤ ሕጉም መዝገቡን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ክሱን ከተመለከተ በኋላ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
ፍርድ ቤቱ በቀረበለትን የክስ መዝገብ ተከሳሽን በ9 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
©️ዳጉ_ጆርናል
Source: Yeneta Tube









No comments yet.