#Ethiopia | የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከሀብታቸው አንድ ሶስተኛውን ለበጎ አድራጎት ስራዎች ለማዋል ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።
የቢሊየነሩ ልጅ ሀሊማ ዳንጎቴ ለብሉምበርግ (Bloomberg) በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገረጹት መላው የዳንጎቴ ቤተሰብ በዚህ ውሳኔ ላይ ሙሉ ድጋፋቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የዳንጎቴ ሀብት ከ35 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት የሚነገር ሲሆን 33 በመቶው ለበጎ አድራጎት ሲውል ከ11 እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ይሆናል።
ይህም በአፍሪካ ታሪክ በግል ባለሀብት ከተደረጉ ትላልቅ የበጎ አድራጎት ስጦታዎች አንዱ ያደርገዋል ነው የተባለው።
ስጦታው በዋናነት በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብአዊ እርዳታዎች ላይ ያተኮሩ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ይውላል ነው የተባለው።
ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው ዳንጎቴ የንግድ አቅማቸውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በሚሰሩበት እና ለልጆቻቸው የኃላፊነት ሽግግር እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nigeria #alekodangote
#Donation
Source: GetuTemesgen









No comments yet.