‎ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር በርናንድ እና ሲ/ር እማዋይሽ ጅምር ሆስፒታል ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ስምምነት አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​በጎንደር ከተማ የተጀመረው የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ጅምር ሆስፒታል ለኢትዮጵያ ህዝብ የጤና አገልግሎትና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኑዛዜ ወራሾች እና ተጠቃሚዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

‎ስምምነት በ2008 ዓ.ም ተጀምሮ የነበረውን ሀገራዊ አላማ ከውልና ማስረጃ እንዲሁም ከእንደራሴው አቶ ዳዊት ደርበው ጋር በመተባበር ዳር ለማድረስ ያስቻለ ምዕራፍ መሆኑ ነው።

‎​በተደረገው ስምምነት መሠረት ሆስፒታሉ የማይሸጥ፣ የማይለወጥ፣ ቅርጽና ይዘቱ ሳይለወጥ እንዲሁም ስመ ንብረቱ ወደ ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይተላለፍ የለጋሾቹ የዘላለም መታሰቢያ ሆኖ እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል።

‎የተከናወነው ስምምነት መሠረት ዩኒቨርሲቲው ህንጻውን አጠናቆ ለህዝብ የህክምና አገልግሎት፣ ለትምህርት እና ለምርምር ማዋል የሚችለውን ጠንካራ መሰረት የጣለ ሲሆን፣ በኑዛዜው የተገለጹት ተጠቃሚዎች መብቶችም ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ተደርጓል።

‎​በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት አፀደወይን ለጋሾቹ ለህዝብ ጥቅም የለገሱት ይህ በጎ አድራጎት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሚሆንና የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ እንዲሁም የህክምና ቱሪዝም የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የወራሾችን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ዳዊት ደርበው እንደገለጹት፣ በዕለቱ የተገኙበት ዋና ምክንያት በሲስተር ማዋይሽ ገሪማ ኑዛዜ መሠረት የተጀመረውን ሆስፒታል አጠናቀው ወደ ተግባር ለማዋል እንደሆነ አስረድተዋል።

እርሳቸውም በኑዛዜው እንደራሴ በመሆን የተሰጣቸውን ሙሉ ስልጣን በመጠቀም ሥራውን ለማስፈጸም እንደተገኙ ገልጸው፣ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሲስተር ማዋይሽ በህይወት በነበረችበት ጊዜ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር አድርጋው የነበረውን ውል እንደገና በማነቃቃት የጀመሩትን ሂደት ለማጠናቀቅ መሆኑን አብራርተዋል።

‎ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኋላም ተሳታፊዎች የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ሙዚየምን እንዲሁም የሆስፒታሉን ጅምር ግንባታ በጋራ ጎብኝተዋል።

‎#GondarUniversity #DrBernardAndSisterEmawesh #Gondar #Ethiopia #Healthcare #MedicalResearch #Legacy #PublicHealth







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: