#Ethiopia | የታዋቂው ድምጻዊ ማይክል ጃክሰን የቅርብ ወዳጅ የሆነው ኮሜዲያን እና ተዋናይ ክሪስ ታከር ስለ ማይክል ልዩ ባህሪ የሚያስታውሰውን ገጠመኝ ወደኋላ በትዝታ ሄዶ ያወሳል።
ማይክል ሰዎች በእጁ የሚገኙ ውድ ቁሳቁሶችን ሲያደንቁለት በስጦታ የመስጠት ልምድ ነበረው ታድያ ይሄን ነገር አጅሬ በቅርብ ርቀት ሲከታተል ቆይቷል፤ ክሪስ ታከር ከዕለታት በአንዱ ቀን የማይክል የክት መኪና ሮልስ ሮይን አደነቀለት ሆኖም የሆነው የተጠበቀው አልነበረም።
ማይክል መኪናውን በስጦታ ከመስጠት ይልቅ ለታከር “አንተ በጣም ቀልደኛ ነህ፤ ሄደህ የራስህን ግዛ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ሙሽሽ አደረገው።
በ “You Rock My World” የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ አብረው ከሠሩ በኋላ የጠበቀ ወዳጅነት የመሰረቱት ሁለቱ አርቲስቶች በመካከላቸው የነበረው ግንኙነት ፍቅርና መከባበር የተሞላበት ነበር።
ክሪስ ታከር ማይክልን ሁልጊዜም በትሕትናውና በሰው አክባሪነቱ የሚያስታውሰው ሲሆን የ”ሮልስ ሮይስ” መኪናው ነገር ግን አሁንም እንደሚከነክነው አልሸሸገም።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.